.png)
ከሊሊ ሞገስ
ያንን ዋሽንት አምጡት ዋ ባይ
ትካዜው ቢለቀኝ
መቼም ያለ ሀሳብ ዋ ባይ
ምንም ዘመድ የለኝ
ዋ ስንቱ ዋ ስንቱ ዋ ስንቱ ዋስንቱ
ልበል በዋሽንቱ
''ኩኩ መለኮቴ'' ከተሰኘው የሙዚቃ አልበሙ ላይ ''ዋ ስንቱ'' የተሰኘችዋን ምርጥ ዜማ ነበር ግጥሟን የቆነጠርኩላችሁ::
የእድሜን እና የትውልድ አመተ ምህረተ ምህረቱን ነገር ለእናቱ ወይም ለአባቱ እንተወው እና ይሁኔ በላይ በአጭሩ የተወለደው በጎጃም ክፍለ ሀገር በፍኖተ ሰላም ከተማ ነው:: ዛሬ የትራንስፖርት ችግሩ በመጠኑም ቢሆን የተቃለለበት ወቅት ይሁን እንጂ በዛ ዘመን ወደ ባህር ዳር አልያም ጎንደር ሲሄዱ አዳር ፍኖተሰላም ነበር:: በፍኖተ ሰላም ግሮሰሪዎች... መንገድ ላይ እና በአጠቃላይ ሆቴል ቤቶች ማስንቆ ያነገቡ ብዙ አዝማሪዎችን አላያችሁም?.... ታለንትድ ከሆኑት እነዚህ ሕጻናት አዝማሪዎች መካከል አሁን ብዙዎቹ ወደሙዚቃው አለም ገበተዋል - ጥቂቶቹ እንደ ይሁኔ በላይ ተሳክቶላቸዋል:: ከቤተሰቦቹ 3 ልጆች የመጨረሻው የሆነው ይሁኔ ከላይ ብዙዎች እንደሚመሰክሩለት ማንነቱን አይረሳም::
የሙዚቃ ፍቅሩና ታለንቱ ወደ ጥብበ የመራችው ብዙዎቹ ''የጎጃም አምባሳደር'' የሚሉት ይሁኔ በላይ ግሽ አባይ ባንድ ውስጥ በመግባት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራት የሙዚቃ ክሊፕ (ሙዚቃዊ ድራማውን) ለሕዝብ አደረሰ::
''አንቱዬዋ'' የተሰኘችው ድራማዊ ሙዚቃ ሰማህኝ በለውን ሳይቀር ያካተተች ስትሆን ለይሁኔ በላይ መታወቅ በሩን የከፈትችለት ዜማ ነበረች:: ግሽ አባይ ባንድ በርካታ የባህል ሙዚቀኞችን ለሕዝብ ያደረሰ ለባህል ሙዚቃችን እድገት ትልቁን ሚና የተጨወተ ስብስብ ነበር::
''በልጅነታችን በግሽ አባይ ውስጥ የምንሰራቸው ሥራዎች የሚገርሙ ነበሩ'' የሚለው ይሁኔ ስለ አንቱዬዋ የሙዚቃ ድራማ አውርቶ አይጠግብም:: ''ፈጠራውን እስከአሁን ድረስም አደንቃለሁ'' የሚለው አርቲስቱ ''ከሕዝብ ጆሮ ዜማዋ ከደረሰች ጊዜ ጀምሮ የእኔ ሕይወት አንድ በአንድ እየተለወጠ መጣ::'' በማለት የሕይወት መስመሩን ይህ ስራው እንደጠቆመው ተናግሯል::
''የእኔ የሙዚቃ ሕይወት የሚጀመረው ከአካባቢ ነው:: ቆላ ደጋ ዳሙት የሚል ፍላጎት ያላቸው ልጆች ስሜታቸውን የሚያስደስቱበት የወረዳ የሙዚቃ ቡድን ነበረ:: እዚያ እየተሰባሰብን ራሳችንን ከማስደሰት አልፎ በአንዳንድ ዝግጅቶች ላይ ሥራዎቻችን ማቅረብ ጀመርን'' የሚለው ይሁኔ የሙያ መሰረቶቹን አንድ በአንድ ያስረዳል:: ''ከዚህ በፊት ግን በትምህርት ቤት ለጓደኞቼ ስዘፍን አስተማሪዬ አይተው አንተ በኢትዮጵያ ውስጥ ታዋቂ ዘፋኝ ትሆናለህ ብለው የሰጡኝ ማበረታቻ ለዛሬው መሰረት ሆኖኛል ይላል::
''እረ ነይ ግቢ ግቢ ግቢ...
አረ ነይ ግቢ ግቢ... አንቺ ልጅ ግቢ ግቢ
እረ ተይ ግቢ ግቢ.... በኔ ሞት ግቢ
ውጡና አነጋግሯት አንድ ሁለት ሆናችሁ
የቆመችበትን ምክንያት ጠይቃችሁ....
እሷ ውጭ ቆማ... በር ተቀምጣ
ማን እህል ሊበላ ማን ማን ውሀ ሊጠጣ
የታለች በር ቆማለች.; አስገቧት አልገባም አለች!!''
‘’ሙሉቀንን ማዳመጥ፤ ማድነቅና የእርሱን መድረክ ውሎን ፊት ለፊት እያየሁ ከሥር ከሥሩ የእርሱን ፈለግ ልከተል፤ እርሱ በዋለበት መድረክ ለመሰማራት ልቤ ተሰቅሎ ደፋ ቀና ስል ከመቅስፈት ከዘፈኑ ዓለም ተሰወረ:: ይሁንና ጋሼ ሙሉቀን አዘፋፈኑ ማለቴ ድምጽ አወጣጡ፤ ግጥምና ዜማ መርጦ በማዋሀድ ያቀርባቸው የነበሩት ዘፈኖቹ ዛሬም፤ ነገም ለእኔም ሆነ ለመላው አድናቂዎቹ መጽናኛ ሆኖናል:: በተረፈ ግን ድምጻዊ ሙሉቀንን የሚተካ ዘፋኝ ይፈጠራል የሚል ግምት የለኝም::’’
ለድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ አድናቂዎች የኢንተርኔት መረብ ይሁኔ በላይ የሰጠውን አስተያየት ነው የቆነጠርኩላችሁ:: ከዚህ የይሁኔ በላይ ንግግር የምንረዳው ለሙዚቃ መሰረቱ ሙሉቀን መለስ እንደሆነ ይሁን እንጂ የይሁኔ የሙዚቃ ሕይወት ስኬት በር ከፋቹ መምህሩ እንደሆኑ በአንድ ወቅት በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አትቷል::
‘I think yehunie's music typicaly show the Gojjam society of Ethiopia.Due to this we admire our beloved singer Yehunie Belay.I hope he also continues with this and satisfy our interest. Long live to our beloved singer Yehunie Belay!’ ጆስ የተሰኘው የመረጃ መረብ ስለ ይሁኔ የተናገረው ነው::
ከሙዚቃ ቡድኑ አልፎ የመጀመሪያ አልበሙን ለሕዝብ ያቀረበው ይሁኔ የአዘፋፈን ስታይሉ ሙሉ በሙሉ ባህል የተላበሰ እና እንቅስቃሴውም ከዘፈኑ ጋር አንድ አይነት በመሆኑ ቶሎ ሕዝብ ሊቀበለው ችሏል::
''ያገሬ ልጅ ባለጋሜ ትውልዷ ጎጃሜ'' የተሰኘችው የይሁኔ የመጀመሪያ አልበም በመላው ኢትዮጵያ የተደመጠ ሲሆን በባህል ሙዚቃ የካሴት ሽያጭም የወቅቱ አንደኛ እንደነበር ይነገራል:: ይህ ሥራው ስኬትን ያጎናጸፈው በትክክልም የጎጃም ''አምባሳደር'' ቢባል የማያንሰው ይሁኔ ''አሎ ሉሎ''ን አልበም አከለ:: ይህም አልበም እንደወጣ የሕዝብ ጆሮ ለመግባት ጊዜን አልፈጀበትም:: ''ብዙዎች እድለኛ ነህ ይሉኛል:: በእርግጥም እድለኛ ነኝ:: በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ቶሎ ሕዝብ ጋር ለመድረስ ችያለሁ'' የሚለው ይሁኔ ለዚህ ሁሉ ስኬቱ ግን ያሳለፈውን ችግር እና መከራ አይዘነጋም:: ''ብዙ ነገሮች በሕይወቴ ውስጥ ደርሰውበኛል:: ሁሉም በእግዚአብሄር ሀይል አልፌ ለዚህ በቅቻለሁ'' ሲል ፈጣሪውን ከምንም በላይ ያመሰግናል::
ይሁኔ 3ኛ አልበም ሲወጣ ስታይሉም እያደገ እንደመጣ አሳየ:: ከባህል ሙዚቃዎች ወጣ ብሎም ወደ አፍሪካ ስልት ሙዚቃዎችም የኢትዮጵያን ባህል አስገብቶ መስራት ጀመረ:: ''ብ..ብ ከፊላው ስር'' የምትባለው አልበሙ የብቃቱን ደርጃ እጅግ አድርጋ ማደጉን ያሳየች አልበም ነበረች::
ይሁኔ ከዛም ኩኩ መለኮቴ የተሰኘውን አልበሙን ሲያወጣ ከአሜሪዋ የወቅቱ ፕሬዚዳንት ከነበሩት የቢል ክሊንተን ባለቤት ሚስ ሂላሪ ክሊንተን ጋር ለመገናኘት እና ካሴቱን በስጦታ ለማበርከት ችሏል:: የሙዚቃ ሥራውን በመጠኑም ቢሆን ከቃኘን ወደ ግል ሕይወቱ ስንመለስ ይሁኔ ከባለቤቱ የሺመቤት (ቱቱ) ጋር በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ውስጥ ከአንድ ወንድ ልጁ እና ሴት ልጁ ጋር በፍቅር ይኖራል:: ይሁኔ ለልጆቹ የኢትዮጵያን ባህል እንዳይዘነጉ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አስታውቆ ብዙ ጊዜ ልጁን የጎጃም ሕጻናት የሚለብሱትን የባህል ካኪ ልብስ እንደሚያለብሰው እና ምንነቱን ጠንቅቆ እንደሚያሳውቀው የቅርብ ወዳጆቹ ይናገራሉ:: ይሁኔ በላይ የልጆቹ ስሞች ፍቅር ይሁኔ እና ሰላም ይሁኔ ይባላሉ:: በአሁኑ ወቅት ይሁኔ ከዘፋኝነቱ ሌላ የተሳካለት ነጋዴም ሆኗል:: በአሜሪካን ሀገር የሚታተም የሎ ፔጅስ አለው:: ይህ የሎ ፔጅስ ታርጌት የሚያደርገው በአብዛኛው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብን ነው:: ...............ሻሎም!! ®
other news:-
ኢትዮጵያውያን ቆንጃጅት በዓለም ላይ ነገሡ
ሚስ ሚሊኒየም ተብላ በኢትዮጵያ አሸንፋ የነበረችው ሞዴል ኪዳን ተስፋሁን የአለማችን ምርጥ የሴቶች ሞዴል 2009 በመባል በስፔን ተመረጠች::
Sukier Models International የተባለው ድርጅት ስፔን ላይ ባዘጋጀው ውድድር ላይ ያሸነፈችው ኢትዮጵያዊቷ ኪዳን 1.8 ሜትር የሚለካ ቁመት አላት:: የ24 አመቷ ኪዳን ካሸነፈች በሗላ በሰጠችው ቃል በሀገራችን እምብዛም ያልተለመደውን የሞዴልነት ሞያ በደንብ ለማጠናከር ጠንክራ እንደምትሰራ ተናግራለች:: ከዚህ ቀደም MISS EARTH ETHIOPIA 2008 ተብላም
ያሸነፈችው ኪዳን በስፔን ማሸነፏ ሀገራችንን ስሟን በመልካም ጎኑ ያስጠራል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጥቂት ወራት በፊት በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነችው ሳራ ኑሩ በጀርመን የሞዴል ውድድር ማሸነፏ የሚታወስ ሲሆን ቆንጆዋ ለሥራ ወደ ኒውዮርክ መዘዋወሯን ኮስሞፖሊታን የተሰኘው ታዋቂው የሴቶች የውበት
መጽሄት ዘግቧል:: የጀርመን ቁጥር አንድ ሞዴል ሆና የተመረጠችው ሳራ ኑሩ ዝናዋ ባመጣላት ጸጋ ከእጅ ስልክ አምራቹ ሶኒ ኤሪክስን ኩባንያ ጋር የማስታወቂያ ውልአድርጋለች፣ በዚሁ መሰረት የሶኒ ኤሪክስን ስልኮች ሲወጡም ሆነ በየቦታው በሚደረገው ማስታወቂያ ሥራ ኑሩ ፈገግ እንዳለች የሚያሳየው ፎቶዋአብሮ ይወጣል። አዲሱ የሶኒ ኤሪክሰን ስልክ ፎቶ የሚያነሳው ሳቅ ሲሉለት ብቻ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ ሳራም ፈገግታዋን እያሳየች ስልኩን ታስተዋውቃለች ማለት ነው።®
ወጋየሁ ደግነቱ አረፈ
"የሰው የእንስሣት የአራዊት… እናት እኮነች መድኃኒት”" በሚል ዜማው የምናውቀው ተወዳጁ ድምጻዊ ወጋየሁ ደግነቱ አረፈ:: ከአባቱ ከአቶ ደግነቱ ጅማ ከእናቱ ከወ/ሮአበራሽ ወዳጆ ጥር 12 ቀን 1940 ዓ.ም. በሀረርጌ ክ/ሀገር በወበራ አውራጃ በጐሮ ጉቱ ወረዲ ልዩ ስሙ መካኒሳ በተባለው ስፍራ ተወልዶ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በሀረር ልዑሌ መኮንን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትሎ በነበረው ልዩ የሙዚቃ ፍቅር የተነሳ መጋቢት 1 ቀን 1955 ዓ.ም. በሀረርጌ ክ/ሀገር ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል በታዳጊነት ዕድሜው ተቀጠረ፡፡ ከ1957 ዓ.ም. ጀምሮ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅና ተፈቃሪ ድምፃዊ ለመሆን የበቃው ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ፤ በ1959 ዓ.ም. ከድምፃዊነቱ በተጨማሪ የሀረር ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል የተወዛዋዥ ቡድን አሰልጣኝ፣ የዜማና የግጥ

ስለእናት በዘፈነው ዘፈን እና 'ፈንዲሻ" በተባለው ሙዚቃው የሚታወቀው ወጋየሁ ከሙዚቃው ጎን በተማረው የህግ ሙያ በጥብቅና ሙያ እስከአረፈበት ጊዜ ድረስ ሲያገለግል ነበር:: ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ለነብሱ ገነትን ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ትመኛለች::®
No comments:
Post a Comment