Monday, August 17, 2009


ቀዩን ቲሸርት በጥቁር መነጽር አድጎ ከ16 ወራት እስራት በሗላ የተፈታው ድምጻዊው ቴዎድሮስ ካሳሁን በታሰረ ወቅት አብሮ ለታሰረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን አክብሮት ገለጸ:: ድምጻዊው ከእስር ከተፈታ በሗላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለምልልስ 'በእስር ቤቱ ከበርካታ መልካም ኢትዮጵያውያን ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፉን' ገልጧል::
በታሰረበት ወቅት ከአድናቂዎቹ የመጡለትንና ሲገለገልበት የነበረ
ውን መጽሀፍት ለማረሚያ ቤቱ ቤተ-መጽሀሐፍት የሰጠው ቴዲ
ያሉትን ልብሶቹን እና ቁሳቁሶቹንም ጠያቂ ለሌላቸው እስረኞች ጋር አከፋፍሏል::
በሐምሌ ወር እናት እና አባቱ ተጋብተው፣ በሐምሌ ወር የተ
ወለደው፣ በሐምሌ ወር ለተወለዱት ለቀዳማዊ ሀይለ ሥላሴ
ዘፍኖ ሁለት ሐምሌዎችን በእስር ያሳለፈው ቴዎድሮስ ካሣሁን
ገርማሞ ጥቅምት 23 ቀን 1
999 ዓ.ም. ከሌሊቱ ሰባት
ሰዓት ከአስር ደቂቃ ሲሆን
በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ
17 ክልል በቤተ መንግሥት
አካባቢ ንብረትነቱ የግሉ
በሆነው ኮድ 2-59868 አ
ዲስ አበባ BMW አው
ቶሞቢል መኪናቸው
ደጉ ይበልጣል የተባለ
እግረኛ ገጭቶ ገድሎ
አምልጧል በሚል
በቀረበበት ክስ
በወቅቱ ቴዲ
አፍሮ በመኪና
ገጭቶ ገድሎ ታል በሚል የተጠረጠረበትን የሟ
ች ደጉ ይበልጣል የሕይወት ታሪክ በወቅቱ “ፎር
ቹን” የተባለ የእንግሊዘኛ ጋዜጣ የሟች አባት አ
ቶ ታምሩ ተፈሪን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሟች ከጎ
ጃም መጥቶ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ከአጎቱ ጋር ይኖር
የነበረ የ18 ዓመት ወጣት ነው። ደጉ መጠጥ ከሚ
ጠጡ ልጆች ጋር በመግጠሙ ቤቱን ጥሎ ለጎዳ
ና ሕይወት ይዳረጋል። ነገር ግን በሣምንት አንዴ
ወይም ሁለቴ ወደ ቤተሰቦቹ በመምጣት ይጠይ
ቃቸው እንደነበር ነው:: ቴዲ በወቅቱ ለአዲስ አድማስ
ና ሪፖርተር ጋዜጣ የሰጠው መልስ “ሰውን የሚያህል ክቡር
ነገር ገጭቼ ላመልጥ አልችልም፣ እኔ ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ቦታ አልነ
በርኩም፣ 'ሰው ገጭቶ አምልጧል' የተባለው ወሬ ሐሰትና ጉዳዩም ክብሬን የሚነካ ነው” ነበር ያለው።
"እኔ ሀገር ውስጥ የገባሁት በጥቅምት 23 ቀን ነው፣ የምኒልክ ሆስፒታል ማስረጃ እንደሚያስረዳው ደግሞ ሟች የሞተው በጥቅምት 22 ቀን ነው።” ብሎ በፍርድ ቤት ሲከራከር የቆየው ቴዲ አፍሮ 6 አመት በከፍተኛው ፍርድ ቤት በተፈረደበት ወቅት "ዳኛው በቅንነት ክሴን አልተመለከቱትም" ሲል መክሰሱ ይታወሳል:: በዚህም የተነሳ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበው ቴዲ እስሩ ወደ 2 አመት ተቀንሶለት በአመክሮ ተፈቷል::በቴዲ አፍሮ ዙሪያ የተጠናቀሩ ዘገባዎችን በውስጥ ገጽ ይፈልጉ።
የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ ድምጻዊው ቴዲ አፍሮ በእስር
ቆይታው ሰለሜ በሚለው የሙዚቃ አልበሙ አንድ ሰአሊ ሥራዬን ተጠ
ቅሟል በሚል የ100 ሺህ ብር ክስ ቢመሰርትበትም ቴዲ በዚህም ክስ
ከዚህ ቀደም ነጻ መውጣቱ ይታወሳል::
ስለ ፍቅርና ስለአንድነት የዘፈነው ቴዲ አፍሮ በተደጋጋሚ ፖለቲከኛ አለመሆኑን ቢገልጽም እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ስለ አንድነት መስበክም ሆነ ማውራት ምን ያህል ጥርስ ውስጥ እንደሚያስገባ የቴዲ ጉዳይ ያሳየናል የሚሉ ተንታኞች በርካታ ናቸው:: ®


No comments: