ZeHabesha's Fan Box
ZeHabesha on Facebook
ZeHabesha's Fan Box
ZeHabesha on Facebook
Blog Archive
►
2009
(6)
►
August
(6)
▼
2008
(11)
▼
December
(11)
ቴዲን የፖለቲካ እስረኛ የሚያስመስሉት 8 ነጥቦች
የጋዜጣችን ፊት ገጽ
'ሴት ያሳደገው ልጅ ከመባል ዘወትር ለማኝ ሆኖ አባቴ ባይጠቅመኝም ይቅር'
ለስለስ ያለች መሳሳም ቁጣን አብርዳ ሰላምን ታሰፍናለች
ሃበሻ በሱዳን
ካንቺ በዲት ኤ.አይቪ እንዳለበት እያወቀ ቢያገባሽ ምን ታደርጊያለሽ?
አፍሪቃውያን እጃቸውን ወደ ባራክ ኦባማ ይዘረጋሉ
በኤደን ባህር በርካታ የውሃ እራት ሆኑ
የውጭ ምንዛሬ እጥረት በኢትዮጵያ ተከሰተ
ኦባማ በድሬደዋ
ቴዲ አፍሮ በአንካሳው ሕግ ጥፋተኛ ተባለ
የኢትዮጵያ ሕዝብም ይፈታ
የኢትዮጵያ ሕዝብም ይፈታ!
ለ484 ቀናት በር በሌለው እስር የቆየው ድምጻዊው ቴዎድሮስ ካሳሁን ወደ በር ያለው እስር ቤት የመፈታቱ ዜና አስደስቶናል:: የኢትዮጵያዊው የሙዚቃ አብዮተኛ ቴዲ መፈታት ጥቅሙ አብሮ ታስሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ሙዚቃንም ይፈታዋል ሲሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች ሲተነትኑ ተደምጧል:: አዎ ቴዲ አፍሮ ከታሰረ ወዲህ፤ የ2 ኤፍ ኤም ራድዮዎች መኖርም ታክሎበት በሀገራችን የሲዲ እና የካሴት ሽያጭ ወርዶ በርካታ የሙዚቃ አሳታሚዎች ሲያማርሩ ተደምጠዋል:: ካሁን በሗላ ቴዲ ተፈቶ የሚሰራው የሙዚቃ አልበም ገበያውን ያንቀሳቅሰዋል የሚል እምነት አለ::
ቴዲ ከእስር ቤት ከተፈታ በሗላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ-ምልልስ ወቅት የተናገረው ነገር ቢኖር 'በቃሊቲ በርከት ያሉ ጥሩ ጥሩ ሰዎች እንዳጋጠሙትና መልካም ጊዜን እንዳሳለፈም ተናግሯል:: ከእነዚህ መልካም ሰዎች መካከል ደግሞ በኢሕአዴግ የታሰሩ የሕሊና እስረኞች እንደሚገኙበት አንጠራጠርም:: በኢሕአዴግ ዘመን ከታሰሩ የሕሊና እስረኞች መካከል ‘’በደህና" ሲለቀቅ ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያው ነው ለማለት እንደፍራለን:: በእርግጥ በደህና መፈታቱን ወይም ምን አይነት ቅድመ ሁኔታዎች እንደተሰጡት ወደፊት ጊዜ የሚፈታቸው ሲሆን ቢያንስ ቢያንስ ግን ቴዲ እንደ ፕሮፌርሰር አስራት ሊሞት ሲል አለመውጣቱም ተመስገን ነው::
ቴዲ አፍሮን ለማስፈታት በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ሲጮኹ፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ቴዲ የፖለቲካ እስረኛ እንደሆነ በመመስከር እንዲፈታ ጭምር ሲታገሉ ነበር:: አሁን ቴዲን ካስፈታን ደግሞ ሌሎች የሕሊና እስረኞችን ለማስፈታትና 'ተቃወምከኝ ብሎ የማሰር" ፖለቲካ በኢትዮጵያ ቀርቶ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን መታገል አለብን::
ከነዚህ ውስጥ አንዷ ደግሞ በግፍ የታሰረችው ብርቱካን ሚደቅሳን ጀምሮ፤ ሰሞኑን ለኢሕአዴግ ሚዲያዎች የወሬ ወፍጮ የሆነው የኦነግ አባል ናቸው ተብለው የታሰሩት እነ በቀለ ጅራታና ሌሎች በኢሕአፓ፣ በአርበኞች ግንባር፣ በግንቦት 7፣ በቅንጅትና በሌሎችም ምክንያት የታሰሩ ንጹሀን የዲሞክራሲ ታጋዮች እንዲፈቱ ትግላችንን የበለጠ ለማጠናከር ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል::
የመለስ ዜናዊ አስተዳደር የሕሊና እስረኞችን በአጠቃላይ አዲሱን የኢትዮጵያን ዓመት በማስመልከት ይፈታል ብሎ ማሰብ ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ቢሆንም ይህንን እንዲያደርግም ግፊት የማድረጉ ሀላፊነት በእኛው እጅ ያለ ይመስለናል::
የሕዝብ ልጅ የሆነውን ቴዲ አፍሮን ፈትቶ ሌሎች ሺሕ ቴዲ አፍሮዎችን በእስር ቤት ያጎረው ኢሕአዴግ በማናለብኝነት የሚያደርጋቸውን የሰብአዊ ጥሰቶች እንዲያቆም ቢመከር አልሰማ ካለ ሰንብቷል:: አምባገነን ሥርአት መሆኑና የሕዝብ ድምጽን የማያከበር መሆኑም ሲነጋ ሁሉም አውቆታል:: ለዚህም ነው አሜሪካኖቹ ፊት የነሱት:: እንደ አፍሪካ ሕብረት መቀመጫነቷ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማም ሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በአፍሪካ በተለያዩ ሀገራት ሲዟዟሩ ኢትዮጵያን ሊያዩዋት ቢገባም ሳያይዋት የቀሩትና መንግሥቱን እርቃኑን ያስቀሩት በዚሁ በአምባገነንታቸው ነው:: ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያት ደግሞ እኛ በውጭ ያለነው ወገኖች በየቀኑ በምናደርገው በሰልፍ፣ በፒቲሽንና በሌሎችም መልኩ ማጋለጦች መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል::
ዛሬ በኢትዮጵያ ከሀገር ወዳድ ፖለቲከኞች ውጭ በሀገራችን መዋዕለ ነዋያችንን አፍስሰን፤ እኛም ተጠቅመን ወገናችንም የሥራ እድል ያግኝ ብለው የንግድ ድርጅት ያቋቋሙ ባለሀብቶች በገበያ ተወዳድረው በሀዜብ መስፍን የሚመራውን የኢሕአዴግ ግዙፍ የንግድ ተቋም በመጣላቸው እየታሰሩ ለመሆኑ ለዚህ መልእክት አንባቢዎች መንገር ለቀባሪው እንደማርዳት ይሆናል:: ሆኖም ግን ለወገናችን የሥራ እድል የፈጠሩ ባለሀብቶችም ካለ አግባብ 'የሙስና" ታፔላ ተለጥፎላቸው ሲታሰሩም ዝም ማለት የለብንም:: የመንግስት ባለስልጣናት እንደፈለጓቸው የፈለጉትን ሲያስሩ፣ ሲፈቱ፣ ሰብአዊ መብቱን ሲጥሱ እኛ ጋር ካልደረሰ ምን ቸገረን ብለን በቸልተኝነት መመልከት የለብንም::
የሀገራችን ሰው ሲተርት "ባልጀራህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ" ነውና ዛሬ የምናውቀው ሲታሰር የነገው ባለተራ እኛም እንደሆንን ማሰብና ከወዲሁ በቃችሁ ልንላቸው ይገባል:: በቀጣዩ ዓመት ይደረጋል በሚባለው "ምርጫም" ትክክለኛ እንደ ጋና ያለ የሚያስቀና ምርጫ ተደርጎ የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ስልጣኑን በሕዝብ ለተመረጠ ፓርቲ አስረክቦ ከእስር እንደማንወጣ የታወቀ ነው:: ይህ ከሆነ ደግሞ በቀጣዩ 5 አመታት በርከት ያሉ ቴዲ አፍሮዎችና በርከት ያሉ ብርቱካን ሚደቅሳዎች እንደሚታሰሩ አንጠራጠር:: ስለዚህ መብታችንን አውቀን ስለመብታችን እንጠይቅ:: ሰዎች ሰብአዊ መብታቸው ሲደፈር፤ ሲንኳሰሱ፤ ሲገለሉ ለምን? ማለት እንጀምር:: ዛሬ ቴዲ አፍሮ በር ከሌለው እስር ቤት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደታሰረበት እስር ቤት ነው የተዛወረው እንጂ እሱም አልተፈታም ማለት እንችላለን:: ላለፉት ዓመታት ታስሮ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብም በነጻ የመናገርና የማሰብ እንዲም የፈለገውን አመለካከት እንዲያራምድ፤ የፈለገውን የፖለቲካ አቋም እንዲይዝ፣ በአጠቃላይ የዲሞክራሲ መብቱ 100% ተክብሮ ይፈታ ዘንድ እንታገል::®
ኢትዮጵያውያን ጀማሪ እንጂ ጨራሾች አይደላችሁም የሚለውን ለመሻር....
Ze-habesha
ሚኔያፖሊስ ሴንት ፖል, ሚኔሶታ, United States
በኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር እና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ብዙ የጻፍን: ወቅታዊ መረጃዎችን ስናደርስ የከረምን: እውነትን ስለያዝን የታሰርን: ታስረን የተፈተንን: የእስር ፈተና ሳይበግረን ስደት የገባን: ስደት ብዙ ፈትንኖን ብዙ አስተምሮ: ብዙ አሳይቶ እዚህ ያደረሰን የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር (ኢነጋማ) አባል የሆንን ጋዜጠኞች ነን:: በተለይ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ እና አሳታሚ የሆነው ሔኖክ አለማየሁ በስደት ከሀገር ወጥቶ በሱዳን: በሊቢያ ብዙ ግፎችንና መከራዎችን የተቀበለና ያሳለፈ ሲሆን በሀገረ ሶሪያ እና በቱርክ ብዙ ሕይወቶችን አሳልፎ እዚህ የደረሰ ነው:: እነዚህ የስደት ታሪኮች አምድ ተሰጥቷቸው በጋዜጣችን ላይ ሕይወት እንዲህ መራራም ጣፋጭም እንደሆነች የሚያሳይ ጽሑፍ ከዚህ እትም ጀምሮ ቀርቧል ይከታተሉት:: ብዙ ጊዜ የውጭ ሀገር ሰዎች ''ኢትዮጵያውያን ጀማሪዎች እንጂ ጨራሾች አይደላችሁም"" ሲሉ ይተቹናል:: ይህን የሚሉበት ምክንያት ጥንት ከዓለም በፊት ሥልጣኔን ወደ ሀገራችን አስገብተን ዛሬ ዓለም የቀደመንን እንደምሳሌ በማንሳት ነው::እናም እናንተም የማንበብ የውዴታ ግዴታችሁን ከተወጣችሁ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ጀማሪ ብቻ ሳትሆን ታሪክ ሠሪም መሆን ትችላለች:: በነገራችን ላይ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ጀማሪ እንጂ ጨራሾች አይደላችሁም የሚለውን ለመሻር ሁላችንም በተሰማራንበት የሥራ መስክም ሆነ የኑሮ አቅጣጫ መታገል: አላማችንን ከግብ የማድረስ የአባቶቻችንን የቆራጥነት መንፈስ እላያችን ላይ ማሳረፍ ይኖርብናል:: እኛም ጀማሪ ብቻ ሳይሆን ጨራሽም ለመሆን ዛሬ አንድ ብለን የጀመርናትን ጋዜጣ እንድታነቡልን ስንጋብዝ በጋዜጣው ላይ የሚወጡ ጽሁፎች በሙሉ የአዘጋጁን አቋም እንደማያንጸባርቁ እንድታውቁልን እንፈልጋለን:: የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር በሚያዘን መንገድ ወገኖቻችንን በማንኛውም መልኩ ለማገልገል መጥተናል:: እንኳን ደህና መጣችሁ በሉን::
View my complete profile
Followers
“መ.ሳ.ሳ.ም ክልክል ነው!”
በመስከረም በቀለ
እኛ ሴቶቹን ለሰላምታ ስንስም እንደው ባህሉን ለመጠበቅ ያህል ቦረሽ ቦረሽ አርገውን ነው የሚሄዱት። ሴትና ሴት ሲሳሙ ግን....
ዳኮታ የሚኖሩ አበሾች አብዛኛዎቹ የሚሰሩት በሬ እየታረደ የሚከፋፈልበት የሥጋ መሸጫ ፋብሪካ ውስጥ ነው። አንደኛው ፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩት ተለቅ ያሉ ሰውዬ ስለ ስራቸው ጠይቄያቸው ደስተኛ እንደሆኑ ነግረውኛል። “እንደውም” አሉ ሲያጫውቱኝ ሥራ ሊሄዱ ሲሉ ሚስታቸውን “ምሳ ቋጥሪልኝ” ሲሏት በብልቃጥ አዋዜ እንደምትሰጣቸው አጫውተውኛል። ሁሌ ፋሲካ ማለትም አይደል? የአሜሪካ አገር የሥራ ባህል ከኛ አገር ጋር በጣም የተለየ ነው ። ከሁሉም ነገር ለኛ የሚከብደን ግን የሽያጭ ሥራ ስንቀጠር ገብያተኛ ሲመጣ “ፈገግ በሉ” የሚሉን ነው። ትዝ ይለኛል የመጀመሪያ ሥራዬ አለቃዬ “ጎበዝ ጎበዝ” ሲለኝ 8፡00 ሰዓት ሙሉ ጥርሴን አግጥጩ ማታ ቤት ስገባ ጉንጩን ስትራፖ ይዞኝ እንደ ቦክሰኛ ጉንጬን ቫዝሊን ተቀብቼ ነው ያደርኩት። ጮክ ብሎ ማውራትም ሌላው ችግር ነው። አሜሪካኖች ጮክ ብሎ አለማውራትን እንደድክመት ያዩታል። እኛ በባህላችን ጮክ ብሎ የሚያወራ ሰው ገገማ ወይም ባለጌ ነው የሚባለው፤ እኛ ቤት ጮክ ብለን የምናወራው ከአሜሪካ ስልክ ሲደውል ወይም ፈተና ወድቀን ስንገረፍ ብቻ ነው። አንድ ቀን አንድ እብድ የሚያክል አለቃዬ…. በነገራችን ላይ እኛ ሰፈር ያሉት እብዶች እንደአጋጣሚ ቀጫጮች ናቸው። ስለዚህ ለምሳሌ ያህል የናንተን ሰፈር እብዶች ተጠቀሙ። አፍንጫዬ ሥር ቆሞ ምራቁን ግንባሬ ላይ እያፈናጠቀ ጆሮዬን በጩኸት ሲቀደው ለሱ ሲያወራ አንድ ሰውዬ ትዝ አሉኝ። ሰውዬ ጆራቸውን ደከም ብሏል። እዚሁ አሜሪካ ለሚኖረው ልጃቸው “እባክህ ጆሮ ላይ ተሰክቶ የሚያሰማ መሳሪያ አለ አሉ “ሄሪንግ ኤድ” የማይሰራውን ገዝተህ ላክልኝ”፤ ልጁም ግራ ተጋብቶ ለምንድን ነው የማይሰራውን የምልክልህ? ቢላቸው እሳቸውም “አይ ልጅ እኔ የ 85 ዓመት ሽማግሌ ነኝ ከአሁን በኋላ ስንት ጊዜ እንደምኖር አላውቅም። አንተንም ባለቀ ሰዓት ከማከስርህ የማይሰራውን ላክልኝና ላርገው እሱን ጆሮዬ ላይ ሲያይ ይሄ ሽማግሌ ጆሮው ችግር አለበት ብለው ጮክ ብለው ያወራሉ አሉ። እኔም ታዲያ ድሮ አንዴ ይሄ ግለሰብ ድምጼ ቀጠን ስላለ ጆሮዬ የማይሰማ መስለው እንዴ ስል ነበር። ካሊፎርኒያ ደግሞ ከ600 በላይ የሚሆኑ አበሾች የሚሰሩበት ካምፓኒ አለ። ጠዋት ጠዋት አበሾች ወደ ሥራ ሊገቡ ሲሉ ካምፓኒው በር ላይ ሰላምታ እየቀያየሩ እየተሳሰሙ ፈረንጆች አላስገባ ስላሏቸው ባለፈው ዓመት የካምፓኒው በር ላይ “No kissing” መሳሳም ክልክል ነው የሚል ሳይን “No Smoking” ከሚለው ጎን ፈጥረዋል። እንደው የከንፈር ሊስትሮ አትበሉኝና ሰላምታ ላይ መሳሳም ከሚወዱት ውስጥ አንዱ ነኝ። የካምፓኒው ችግር ከወንዶች የመጣ አይመስለኝም። እኛ ሴቶቹን ለሰላምታ ስንስም እንደው ባህሉን ለመጠበቅ ያህል ቦረሽ ቦረሽ አርገውን ነው የሚሄዱት። ሴትና ሴት ሲሳሙ ግን በተለይ አንዳንዶቹ በእያንዳንዱ መሳሳም መሃል የፉገራ ወሬ ያወራሉ። “የጠፋ ሰው” ሳም ዛሬ ደግሞ በጠዋቱ ፏ ብለሻል፤ ሳም…. ፀጉርሽ ደግመሽ ተቀባሽው እንዴ?”…. ሳም… የኔ ስልክ ነው ወይስ ያንቺ የሚጮኸው?” ሳም።…..®
Thursday, December 4, 2008
የጋዜጣችን ፊት ገጽ
No comments:
Post a Comment
Newer Post
Older Post
Home
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment